በኢትዮጵያ 11 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

3 Yrs Ago
በኢትዮጵያ 11 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 4,225 የላቦራቶሪ ምርመራ 11 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 317 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 5ቱ ወንዶች 6ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡ እድሜያቸውም በ17 እስከ 45 ዓመት መካከል የሚገኙ ናቸው፡፡

ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው መካከል 4 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 6 ከሶማሌ ክልል (ጂግጂጋ ለይቶ ማቆያ) እንዲሁም 1 ሰው በአማራ ክልል (ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ላይቶ ማቆያ) ነው።

ከታማሚዎቹ መካከል 7ቱ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 3ቱ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበራቸው፣ አንዱ ደግሞ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

እስከ ዛሬ ድረስ በጥቅሉ ለ57 ሺህ 254 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top