በዓለም በአንድ ቀን የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ተመዘገበ

14/09/2020 06:13
በዓለም በአንድ ቀን የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ተመዘገበ

 

በትናንትናው እለት በአንድ ቀን በዓለም በኮሮና የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበ ሲሆን፣ በቀኑ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 307 ሺህ 930 ነው፡፡

ይህ ቁጥር እስከ አሁን በአንድ ቀን የተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል፡፡

በእለቱ በበሽታው 5 ሺህ 500 ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ በአጠቃላይ እስከ አሁን በወረርሽኙ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 917 ሺህ 417 ደርሷል፡፡

ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበው በሶስት አገራት ሲሆን፣ በህንድ 94 ሺህ 372፤ በአሜሪካ 45 ሺህ 523፤ በብራዚል ደግሞ 43ሺህ 718 ሰዎች በዕለቱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በአውሮፓ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የዓለም ጤና ድርጅት መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ግብረመልስ
Top