ሩሲያ፣ ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን ከተቀላቀሉ “ከባድ መዘዝ”እንደሚያስከትል አስጠነቀቀች

2 Yrs Ago
ሩሲያ፣ ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን ከተቀላቀሉ “ከባድ መዘዝ”እንደሚያስከትል አስጠነቀቀች

ሩሲያ፣ ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን ከተቀላቀሉ “ከባድ መዘዝ”እንደሚያስከትል አስጠነቀቀች

ኔቶ ዩክሬንን በአባልነት ለማስገባት ከጫፍ መድረሱን ተከትሎ ኔቶ እና ሩሲያ ተፋጠዋል፡፡

ሩሲያ በቅርቡ ኔቶ ከምስራቃዊ አውሮፓ ሀገራት ለቆ እንዲወጣ አስጠንቅቃ ነበር

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊንላንድና እና ስዊድን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት(ኔቶ)ን እንዳይቀላቀሉ እያስጠነቀቀች ነው፡፡

 የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ “ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶ መቀላቀላቸው በጣም ግልፅ ነው…የሩሲያን ምላሽ የሚጠይቅ ከባድ የሆነ ወታደራዊና የፖሊተካ መዘዝ ያስከትላል”ብለዋል፡፡

"በተለምዶ በስቶክሆልም እና በሄልሲንኪ የሚተገበረው የየትኛውም ህብረት አካል ያለመሆን ፖሊሲ በሞስኮ በሰሜናዊ አውሮፓ መረጋጋትን ለማረጋገጥ እንደ አንድ ጠቃሚ ነገር ነው የሚታየው" ሲሉ ዛካሮቫ ገልጸዋል፡፡

አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሀገራት ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረገች ነው የሚል ክስ ሲያቀርቡ፣ ሩሲያ በአንጻሩ ምእራባውያን ሀገራት በዩክሬን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ያሳስበኛል የሚል ክስ በማቅረብ ላይ ትገኛለች፡፡

ሩሲያ ቀደም ሲል የዩክሬን አካል የነበረችውን ክሪሚያን ማጠቃለሏ በምእራብ ሀገራት ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡

ሩሲያ በቅርቡ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ኔቶ ከምስራቃዊ አውሮፓ ሀገራት ለቆ እንዲወጣ አስጠንቅቃ ነበር፡፡

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ወይም ኔቶ ዩክሬንን በአባልነት ለማስገባት ከጫፍ መድረሱን ተከትሎ ኔቶ እና ሩሲያ ተፋጠዋል፡፡

ዩክሬን የኔቶ አባል ከሆነች የደህንነት ስጋት አለኝ በሚል በጉዳየ የተበሳጨችው ሩሲያ ሉዓላዊነቴን ለማስከበር ስል እርምጃ ለመውሰድ እገደዳለሁ በሚል ማስጠንቀቋ ይታወሳል፡፡የሩሲያን ማስጠንቀቂያ ተከትሎም አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ሩሲያ ዩክሬንን ልትወር ትችላለች በማለት ላይ ሲሆኑ በምስራቃዊ አውሮፓ እና አካባቢው ውጥረት ነግሷል፡፡

ሩሲያም በአካባው የተፈጠረው ውጥረት እንዲረግብ ከተፈለገ ኔቶ በምስራቃዊ አውሮፓ በተለይም በቀድሞ የሶቪየት ህብረት አባል ሀገራት ስር በነበሩ ሀገራት ውስጥ ያሰማራውን ጦር ለቆ እንዲወጣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል አስጠንቅቃለች፡፡

ሩሲያ ከዚህ በተጨማሪም ከኔቶ አባል ሀገራት ጋር በጄኔቭ በየትኛውም ቦታ ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሰርጊ ሪያብኮቭ ገልጸዋል፡፡

 

 

 

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top