የደቡብ ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ሳቢያ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

20/01/2022 11:32
የደቡብ ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ሳቢያ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

 

የደቡብ ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ሳቢያ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጓል፡፡

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው የተመራ ልዑክ የ5 ሚሊየን ብር የአይነት እና የ15 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ አስረክቧል።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው ድጋፉን ባበረከቱበት ወቅት የሶማሌ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ፀንታ እንድትቆም እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ የሚያስመሰግነው መሆኑን ጠቁመው፣ በዚህ ማህበረሰብ ላይ ያጋጠመ ችግርን ለመቅረፍ መላው ኢትዮጵያውያን እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ለተደረገው ድጋፍ በሶማሌ ክልል ህዝብ እና መንግስት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ኢትዮጵያውያን እያደረጉ ያሉት ርብርብ ለሶማሌ ህዝብ ያላቸውን አጋርነት ያሳየ ነው ብለዋል።

ይህ የመተባበር ስራም ኢትዮጵያውያን እርስ በራስ እንዲቀራረቡ ያስችላል ብለዋል አቶ ሙስጠፌ።

በክልሉ የተከሰተው የዝናብ እጥረት ላለፉት 40 ዓመታት ያልታየ መሆኑን ያነሱት አቶ ሙስጠፌ ፣የክልሉ መንግስት እስካሁን ባደረገው ርብርብ የዝናብ እጥረቱ ከድርቅ ወደ ረሀብ እንዳይሸጋገር ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በቴዎድሮስ ታደሰ

ግብረመልስ
Top