“የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለምናደርገው ጥረት የከበረውን አግሪኮላ ሜዳልያ ስለተጎናፀፍን ምስጋናዬን ለመግለፅ እወዳለሁ“ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

3 Mons Ago
“የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለምናደርገው ጥረት የከበረውን አግሪኮላ ሜዳልያ ስለተጎናፀፍን ምስጋናዬን ለመግለፅ እወዳለሁ“ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት የተመድ የምግብ እና የግብርና ድርጅት የከበረውን አግሪኮላ ሜዳልያ ስላጎናፀፈ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በሮም ጣልያን በተሰናዳ ክብረ በዓል የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል።

ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት፣ ብሎም ፈጣን፣ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት  የተበረከተ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ለተመድ የምግብ እና የግብርና ድርጅት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለምናደርገው ጥረት የከበረውን አግሪኮላ ሜዳልያ ስላጎናፀፈን ምስጋናዬን ለመግለፅ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

ከፍ ያለ ጠቀሜታ ባላቸው እና የኢንዱስትሪ ግብዓት በሆኑ የግብርና ምርቶች ላይ ትኩረት መደረጉ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እያስገኘ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

የምግብ ሉዓላዊነት ጉዟችንን በፅናት እናስቀጥላለን ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top