የስነ-ምግባር ጥሰት ፈጽመዋል በተባሉ አመራር እና ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ

3 Mons Ago
የስነ-ምግባር ጥሰት ፈጽመዋል በተባሉ አመራር እና ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ
የኢትዮጵያ አሌክትሪክ አገልግሎት የስነ-ምግባር ጥሰት ፈጽመዋል በተባሉ አመራር እና ሰራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን መውሰዱን አስታወቀ።
 
አገልግሎቱ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ የተጠያቂነት ስርዓትን ለማስፈን ባከናወነው ስራ እርምጃው መወሰዱን ነው የገለጸው።
 
ተቋሙ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ከደንበኞች ከቀረቡለት 63 ጥቆማዎች ውስጥ የማጣርት ስራ በማከናወን፤ በ23 አመራር እና ሰራተኞች ላይ ላይ ከጹሑፍ ማስጠንቂያ እስከ ስንብት የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን መውሰዱን አስታውቋል።
 
በተጨማሪም በተቋሙ በውስጥ የስነምግባር ችግር በታየባቸው 409 ሰራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንደወሰደም ገልጿል።
 
በዚህም በ106 ሰራተኞች ላይ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣በ282 ሰራተኞች ላይ የደመወዝ ቅጣት፣ በ11 ሰራተኞች ላይ ስንብት እንዲሁም በ10 ሰራተኞች ላይ ባደረገው ማጣራት ነጻ እንዳላቸው ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
 
ተቋሙ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎች እና ጥቆማዎችን ለመቀበል ከተዘረጉ የ905 እና 904 ነጻ የጥሪ ማዕከላት በተጨማሪ፤ ደንበኞች ቅሬታቸውን ቀላልና ምቹ በሆነ መንገድ ማቅረብ የሚችሉበት ዘመናዊ የሙስና ጥቆማ መቀበያ ስርዓት ለመዘርጋት በሂደት ላይ መሆኑን ጠቁሟል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top