በመኖሪያ ቤት ውስጥ የጦር መሳሪያ እና ከ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ሸሽገው የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

2 Mons Ago
በመኖሪያ ቤት ውስጥ የጦር መሳሪያ እና ከ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ሸሽገው የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በመኖሪያ ቤት ውስጥ የጦር መሳሪያ እና ገንዘብ ሸሽገው የተገኙ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የቀጨኔ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በጦር መሳሪያ ዝውውር በሚጠረጠር ግለሰሰብ ላይ ክትትል በማድረግና ማስረጃ በማሰባሰብባ በክፍለ ከተማው ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጨፊ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የግለሰቡ መኖሪያ ቤት ውስጥ በህግ አግባብ ባደረገው ብርበራ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያና በህገ ወጥ መንገድ የተከማቸ ገንዘብ ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በግለሰቡ መኖሪያ ቤት በተደረገ ብርበራ አንድ ኤስ ኬ ኤስ ጠብ መንጃ ከመሰል 30 ጥይት ጋር፣ አንድ ክላሽ ኮቭ ከ72 ጥይት እና አንድ ኮልት ሽጉጥ ከ8 ጥይት ጋር እንዲሁም 1 ሚሊዮን 294 ሺህ 700 ብር እንደተገኘ ተጠቅሷል።

በተመሳሳይ በዚሁ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ሩፋኤል እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ አድረጎ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል ባካሄደው ብርበራ አንድ ክላሽ ኮቭ ጠብ መንጃ ከ90 መሰል ጥይት እና ሁለት ኮልት ሽጉጥ ከ29 ጥይት ጋር በኤግዚቢትነት ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ፖሊስ ጣቢያው ጨምሮ ገልጿል፡፡

ወንጀለኞች ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያን በመጠቀም ሊፈፅሙ የሚያስቡትን ወንጀል አስቀድሞ ለማክሸፍ መረጃን መነሻ በማድረግ የሚያከናውነውን ጠንካራ የቁጥጥር ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top