የግብርናው ዘርፍ ላይ መዋቅራዊ ሽግግር በማድረግ ድህነትን መቀነስ የመንግስት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

12 Days Ago
የግብርናው ዘርፍ ላይ መዋቅራዊ ሽግግር በማድረግ ድህነትን መቀነስ የመንግስት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ነው -  አቶ ተመስገን ጥሩነህ

የግብርናው ዘርፍ ላይ መዋቅራዊ ሽግግር በማድረግ ድህነትን መቀነስ የመንግስት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ሀገራዊዉ የሌማት ትሩፋት የአንድ ዓመት ተኩል አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ግብርናውን ከበሬ እርሻ ወደ ተቀናጀ ግብርና ቴክኖሎጂ ለማሻገር ከመንግስት ባለፈ የግሉ ዘርፍ እና ምርምሩ ሰፊ ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በሌማት ትሩፋት ምርትን ማሳደግ፣ የውጭ ምርትን በሀገር ውስጥ መተካት እና በዘርፉ የስራ ዕድል ፈጠራ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የሌማት ትሩፋቱን ውጤታማ ለማድረግ በባለሙያዎች እና በአመራሩ የሚደረገው ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ተጠቁሟል ።

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ባከናወነቻቸው ተግባራት በአለም አቀፍ ተቋማት ጭምር ዕውቅና አግኝታለች ያሉት የግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ፤ ኢትዮጵያ ያላትን የእንስሳት ሀብት ጸጋ በአግባቡ እንዲትጠቀም በሌማት ትሩፋት መርሃግብር የተፈጠረውን ዕድል መጠቀም የግድ ነው ብለዋል።

ባለፉት ጊዜያት በሌማት ትሩፋት መርሃግብር ከዕቅድ በላይ የሆነ አፈፃፀም የተመዘገበ ቢሆንም ከክልል ወደ ክልል ያለውን የአፈፃፀም ልዩነት ለማጥበብ በዘርፉ ያለውን የግብዓት አቅርቦት ችግር ለመፍታት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በመድረኩ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እና ሌሎች የፌደራል እና የክልል የስራ ሀላፊዎች እየተሳተፉ ነው።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top