አንቶኒ ብሊንከን ሩስያ በአፍሪካ ያላትን ተፅዕኖ ለመመከት ያለመ ጉብኝታቸውን ጀመሩ

1 Yr Ago
አንቶኒ ብሊንከን ሩስያ በአፍሪካ ያላትን ተፅዕኖ ለመመከት ያለመ ጉብኝታቸውን ጀመሩ
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሩስያ በአፍሪካ ያላትን ተፅዕኖ ለማሳደግ የምታደርገውን የዲፕሎማሲ ጥረት ለመመከት ያለመ ጉብኝት ጀመሩ። ብሊንከን በዚህ ጉብኝታቸው ወደ ሦስት የአፍሪካ አገራት እንደሚጓዙ ይጠበቃል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከደቡብ አፍሪካ በኋላ ወደ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ቀጥሎ ደግሞ ወደ ሩዋንዳ ይሄዳሉ ተብሏል። የብሊንከን የመጀመሪያ መዳረሻ የሆነችው ደቡብ አፍሪካ በዩክሬኑ ጦርነት ሞስኮን ለማውገዝ የምዕራባውያንን ጥሪዎች ሳትቀበል ገለልተኛ ሆና መቆየቷን ቢቢሲ ዘግቧል። ከሁለት ሳምንታት በፊት የሩስያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ስድስት ቀናትን በፈጀ ጉብኝት አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ተለያዩ አገራት ተጉዘው ነበር።
ላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በግብጽ ጀምረው ቀጥሎም ወደ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ዩጋንዳ እና ኢትዮጵያ ተጉዘው ከባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዋል። በቆይታቸውም በተለይም በዩክሬኑ ጦርነት ምክንያት በአፍሪካ በተከሰተው የስንዴ አቅርቦት እጥረት ላይ ትኩረት ሰጥተው ንግግሮችን አካሂደው ለምግብ እጥረቱ ተጠያቂዎቹ ምዕራባዊያን አገራት ናቸው ሲሉም ተደምጠዋል። "ምዕራባውያን አገራት የበላይነታቸውን በሌሎች ላይ ለመጫን እየሞከሩ ነው" ሲሉም ከሰዋል። እንዲሁም ሞስኮ የዓለምን የምግብ ቀውስ አስከትላለች የሚለውን ወቀሳ አጣጥለውታል። ሩስያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት የአረቡ ዓለም አገራት እና አፍሪካ በእህል አቅርቦት እጥረት ክፉኛ ተጎድተዋል።
 
 
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top