የቻይናን የባሕር ላይ የድንገተኛ ሕክምና እና የነፍስ አድን አቅም ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ተብሎ የሚጠበቀው እና በውኃ ላይ ዝቅ ብሎ የሚበር የነፍስ አድን ተሽከርካሪ የሙከራ በረራ በስኬት በማጠናቀቅ አዲስ ታሪክ አስመዝግባለች።
ይህ ልዩ የቴክኖሎጂ ውጤት በውኃ አካል ላይ በጣም ዝቅ ብሎ በመብረር ከፍተኛ ፍጥነትና መረጋጋት ያለው ጉዞ ማድረግ የሚችል ነው።
ተሽከርካሪው በዘመናዊ የባሕር ላይ ኢንተርኔት የተገጠመለት በመሆኑ፣ በነፍስ አድን ጉዞ ላይ እያለ የሕክምና መረጃዎችን በቀጥታ ለስፔሻሊስት ሐኪሞች የማስተላለፍ፣ የሕክምና መሣሪያዎችን በሩቅ ሆኖ የማንቀሳቀስ እና የሕክምና ምክክሮችን የማድረግ አቅም አለው።
ይህም በባሕር ላይ አደጋ ሲያጋጥም ፈጣንና የተሟላ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል።
የቻይናን የባሕር ላይ የድንገተኛ ሕክምና እና የነፍስ አድን አቅም ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ተሽከርካሪ፣ በቅርቡ የሙከራ በረራውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል።
በአንድ ጊዜ እስከ አምስት የሚቀመጡ ወይም ሦስት በቃሬዛ ያሉ ታካሚዎችን መጫን የሚችለው ይህ ተሽከርካሪ፣ ሁለት ነርሶች፣ አንድ ሐኪም እና አንድ አብራሪ የያዘ መደበኛ የሥራ ቡድን ይኖረዋል።
ይህ ስኬት ቻይና በዓለም አቀፍ ደረጃ በባሕር ላይ የሕክምና ድጋፍና የነፍስ አድን ስራ ያላትን አቅም በከፍተኛ ደረጃ የሚያጎላ ሆኖ ተመዝግቧል።
በሃና ምንዳሁን