Search

የቻይና እና አፍሪካ የምርምር ማዕከል ሥራ ጀመረ

ዓርብ ኅዳር 11, 2019 106

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያቋቋመው የቻይና እና አፍሪካ የምርምር ማዕከል በይፋ ሥራ ጀመረ።

ማዕከሉ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ላይ ትኩረት በማድረግ ዋና ዓላማውን የዕውቀት ልውውጥ ማሳደግና የጋራ ትብብርን የሚያጠናክሩ ጥናቶችን ማካሄድ አድርጓል።

ይህም በቻይና እና በአፍሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ከማጠናከሩም ባሻገር የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ተመላክቷል።

በአዲስ አበባ በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ጂያንግ ፌንግ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ሰለሞን አብርሃ እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፕሮፌሰር ማቴዎስ እንሰርሙ ተገኝተዋል።

በሳዳት መሐመድሳኒ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: