Search


ከታች በተቀመጠው ቅፅ መሰረት የግል መረጃዎችን ይሙሉ፡፡ በቡድን መወዳደር ለሚፈልግ አንድ ተወካይ በመምረጥ በተወካዩ በኩል መመዝገብ ይኖርበታል፡፡ በቁጥር የሚፈለጉ መረጃዎች በቁጥር ብቻ መሞላት አለባቸው፡፡ የገንዘብ መጠኖች ሁሉም በብር የተጠየቁ ናቸው፡፡ ይህ ምዝገባ ለአንድ ምዕራፍ ወይም ለሶስት ወራት የውድድር ጊዜ የሚያገለግል ነው፡፡ ይህ የሥራ ፈጠራ ውድድር በኢቲቪ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ ሲሆን በሶስት ወራት ውስጥ የተለያዩ የቀረፃ ኘሮግራሞች ይኖሩታል። ኘሮግራሙ በየሳምንቱ በቴሌቪዠንና በሶሻል ሚዲያ ይተላለፋል። የውድድሩ መስፈርቶች የቢዝነሱ ፈጠራ፣ ችግር ፈቺነት፣ አዋጭነት፣ የአተገባበር አመቺነት፣ የካፒታል ተመጣጣኝነት እና የገበያ ተፈላጊነት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ በዚህ ውድድር ላይ የስራ ፈጠራ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ሊሳተፍ ይችላል፡፡ ወጣቶች ይበረታታሉ፡፡ በውድድሩ ለመመዝገብ የሚያስፈልገው የውድድሩን ቅፅ ኦን ላይን መሙላት ነው። በውድድሩ ለመሳተፍ ቀጣዩን የመወዳደሪያ ቅፅ የሚጠይቃቸውን መረጃዎች ማሟላት ያስፈልጋል፡፡


የግል መረጃ/Personal Info

የሚወዳደሩበት ፕሮጀክት ሀሳብ (ከ100 ቃላት ያልበለጠ)

Proposal of the project for which you are competing (no more than 100 words)


የስራ ሀሳብዎ ገበያና ትርፍ ምን ያክል ነው

What is the market and profit potential of your business idea? (No more than 100 words.)


ፕሮጀክቱ የሚጠይቀዉ የካፒታል መጠን

Specify the capital needed for the project


ማስታውሻ፡- ይህ የውድድር ምዝገባና ቀጣይ የምልመላ ምዕራፎች በዲጂታል ስርዓት ብቻ የሚፈፀሙ ናቸው፡፡ ከላይ በተጠቀሱት የውድድር መስፈርቶች መሰረት ተወዳድረው ያለፉ እጩ ተወዳዳሪዎች በዚህ ድረ-ገፅ ይፋ ይሆናሉ፡፡ የቅፁ ሁሉም ክፍሎች በመመሪያዎቹ መሰረት መሞላት አለባቸው።