Search

የመደመር አንቀጽ

ረቡዕ ሰኔ 03, 2018 82

የመደመር ነገ - ትውልድ ነው። እርግጠኛው ሀገር የመገንቢያ መንገድም ትውልድን በማነጽ ውስጥ ያለው ምሥጢር ነው። የዛሬ መልካም ውጤቶችና እሴቶች ቀጣይነት የሚረጋገጠው በትውልድ ውስጥ ሲሠርጹ ነው።
የመደመር ግብ ሀገር የሚያጠነከር እሴትና ባህል መገንባት ስለሆነ፤ ራሱን ትውልድ የሚግባባበትና የሚነጋገርበት ቋንቋ ለማድረግ ይተልማል። በፍቅር፣ በወንድማማችነትና በኅብር የሚግባባ ትውልድን ለማነጽ።
መደመር የዛሬን ትውልድ ዐቅም በማሰባሰብ፣ ካለፈው ትውልድ የወረሳቸውን ጥንካሬዎች በማሳደግ፣ እንዲሁም ከፍተቶችን በማረም፣ የቀጣዩን (የመደመር) ትውልድ የምንመለከትበት የሃሳብ መነጽርና የመግባቢያ ሰነዳችን ነው፡፡ ይህ የትውልድ ግንባታ እውን እንዲሆን፤ በተገዳዳሪ አፍራሽ እይታዎች (ፓራዳይሞች) ውስጥ የመደመር ዕይታንና እሴትን ያለማሰለስ በትጋት ማሥረጽና ማጠናከርን ይጠይቃል።
የመደመር ትውልድ
ገጽ - መግቢያ