Search

በማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ኢንጂነር ሐና ብርሃኑ

ማክሰኞ ሰኔ 16, 2018 26

በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ከነበረበት ደካማ አፈጻጸም ተነስቶ አሁን ላይ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አንዱ መሆን የቻለበትን የማዕድን ትራንስፎርሜሽን ጉዞ አቅርበዋል።

በቁርጠኛ ማሻሻያዎች፣ በገበያ መልሶ ማዋቀር እና እሴትን መጨመር በሚያስችሉ ኢንቨስትመንቶች በመታገዝ ዘርፉ ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢን እያስገኘ፣ የገቢ ምርቶችን ጥገኝነት እየቀነሰ እና ለኢንዱስትሪ ልማት አዳዲስ ዕድሎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ ኢንጂነር ሐና አመላክተዋል።

በወርቅ፣ በወሳኝ ማዕድናት፣ በነዳጅ እና በማዳበሪያ ምርት ላይ እየተስፋፋ በመጣው የኢንቨስትመንት ለውጦች፣ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት አቅም ወደ ተጨባጭ ብሔራዊ ዕድገት እየቀየረችው ትገኛለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ እነዚህ ስኬቶችም በሀገር በቀል ቅኝት የሪፎርም ማሻሻያ፣ በገዘፈ ርዕይ እና አፈጻጸም ድምር ውጤት እንደሚያስገኙ ህያው ማረጋገጫዎች ናቸው።