Search

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት

ሰኞ ሐምሌ 06, 2018 169

የከተማችን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በከተማችን ተቋማት ላይ ያዘጋጀው የሥራ አፈጻጸም እና የኦዲት ሪፖርት ላይ ለምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

የኦዲት ሪፖርቱ የሸፈነው 107 የመንግስት ተቋማትን ሲሆን፣ የኦዲት አገልግሎት አይነቱ የፋይናንስ እና ህጋዊነት ኦዲት፣ ክዋኔ ኦዲት፣ የገቢ ኦዲት፣ የአካባቢ ኦዲትና የማጭበርበር ወይም ልዩ ኦዲት ናቸው።

የኦዲት ሥራው ዓለም አቀፍ የኦዲት ደረጃዎችን እና የኢትዮጵያ መንግሥት የሂሳብ አያያዝ ስርዓትን ተከትሎ እያከናወነ ነው ።

በዚሁ አግባብ ግኝቶቹ:-

ከንቲባ ጽ/ቤትን፣ ሥራና ክህሎት ቢሮንና ፕላንና ልማት ቢሮን ጨምሮ በ26 ተቋማት በተደረገው ኦዲት የተቀመጡትን የሂሳብ አያያዝ ደረጃዎችና አሰራሮችን ጠብቆ ምንም ነቀፌታ ያልተገኘባቸው፤ 49 ተቋማት ጉልህ ነቀፌታ ያልተገኘባቸው በመሆኑ በአጠቃላይ ኦዲት ከተደረጉት 70 % ሲሆኑ፤ 31 ተቋማት በተለይም የወረዳ ጽ/ቤቶችና ኮሌጆች የሂሳብ አያያዛቸው ችግር ያለበት መሆኑን የኦዲት ሪፖርት ግኝቱ ያሳያል።

በከተማችን የህዝብን ሃብት እና ንብረት እንዳይባክን፣ በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የኦዲት መስሪያ ቤቱ የክትትል ስራዎች በጥንካሬ የሚወሰድ ነው።

በኦዲት ግኝት መሰረት መታረም የሚገባቸውን እያረሙ፤ የአቅም ችግር ያለባቸው የፉይናንስ ሰራተኞችን በአቅም ግንባታ እንዲደገፉ ማድረግና የኦዲት ማጠናከር እንዲሁም ተቋማት ላይ ቀጣይ ክትትልና እርምት እየተወሰደባቸው የሚኬድ ይሆናል።

ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት በአጠቃላይ የከተማዋ ገቢና ወጪ ጤናማ መሆኑን አረጋግጧል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: