Search

አረንጓዴ ዐሻራ፡ በኢትዮጵያውያን ዘንድ አዲስ የኅብረት እና የጋራ ዓላማ ባህልን የፈጠረ መርሐ-ግብር

ረቡዕ ሐምሌ 22, 2018 51

ኢትዮጵያ 2011 . በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) አነሳሽነት የጀመረችው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ዛሬ ላይ የኢትዮጵያን ገጽታ ከመስዋብ አልፎ የምግብ ዋስትና እና የዲፕሎማሲ አቅም የለወጠ ታላቅ ሀገራዊ እና አህጉራዊ ንቅናቄ ሆኖ ታይቷል።

ባለፉት ሰባት ዓመታት የተመዘገቡት ስኬቶች ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ላይ ያሳየችውን ተግባራዊ ምላሽ እና ያስመዘገበችውን ዘላቂ ፍሬ በጥልቀት የሚያስረዱ ናቸው።

ከሥነ ምህዳር እና ተፈጥሮ ጥበቃ አንጻር ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ 48 ቢሊዮኖች በላይ ችግኞችን በመትከል ምድርን ለማከም ተችሏል። ይህም የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ከነበረበት ዝቅተኛ ደረጃ በማስወጣት በአጭር ጊዜ ውስጥ የደን ሽፋኗ እንዲያገግም አስችላል።

በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ ዘመቻ የአፈር መሸርሸርን ከመቀነስ፣ የከርሰ ምድር ውኃን ከማጎልበት እና የተጎዱ የሥነ ምህዳር ክፍሎችን መልሶ ከመገንባት አንጻር እጅግ የጎላ ሚና ተጫውቷል።

ቀደም ሲል በድርቅ እና በአፈር መሸርሸር የተጠቁ አካባቢዎች ዛሬ ላይ አረንጓዴ ለብሰው በማገገም ይገኛሉ።

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከተራ የተፈጥሮ ጥበቃ ባለፈ ወደ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ምንጭነት ተሸጋግሯል። በተለይም ባለፉት ዓመታት ትኩረት የተሰጣቸው የተቀናጁ የፍራፍሬ (አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ብርቱካን) እና የቡና ችግኞች ተከላ ዐበይት ውጤቶችን እያስገኙ ይገኛሉ።

ይህም ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ አባወራዎች አዲስ የገቢ ምንጭ ከመፍጠሩም በላይ በሀገር ውስጥ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ለውጭ ገበያ የሚላኩ ምርቶችን በማሳደግ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማጠናከር ትልቅ መሠረት ጥሏል።

መርሐ-ግብሩ በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ አዲስ የኅብረት እና የጋራ ዓላማ ባህልን ፈጥሯል።

እድሜ፣ ጾታ፣ የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት ሳይበግረው በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሚሊዮኖች ዜጎች በአንድ ጀምበር ወጥተው ችግኝ የመትከል ልምድን ማዳበራቸው ሀገራዊ አንድነትን እና የመረዳዳት መንፈስን አጠናክሮታል።

ይህም ኢትዮጵያውያን በትብብር ከተነሱ የማይሻገሩት ፈተና እንደሌለ በተግባር ያሳዩበት ታላቅ ማኅበራዊ ሀብት ሆኗል።

የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ የሀገር ወሰንን ተሻግሮ ለአጎራባች ሀገራት ችግኞችን በማካፈል የቀጣናዊ ትስስር እና አረንጓዴ ዲፕሎማሲ ማሳያ መሆን ችሏል።

የአየር ንብረት ለውጥን ለመመከት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የፖለቲካ መሪዎች በሚታገሉበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ በተግባር ያሳየችው ይህ ንቅናቄ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሙገሳ እና ዕውቅና እንድታገኝ አድርጓታል።

ባለፉት 7 ዓመታት የተካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዞ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ በምግብ እራስን መቻል፣ በሕዝባዊ አንድነት እና በዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ያስመዘገበችው ድል ነው።

ኢትዮጵያውያን ይህን የተተከለውን ተስፋ ጠብቀው በማሳደግ እና ወደ ተሻለ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በመቀየር ለቀጣዩ ትውልድ አረንጓዴ፣ የተረጋጋች እና የበለፀገች ሀገርን ለማስረከብ ተሰናድተዋል። 

በሃና ምንዳሁን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: