Search

“የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎች ለአጭር ጊዜ እፎይታ ተብሎ በአንድ ወገን ፍላጎት መመለስ አይቻልም” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዓርብ ሐምሌ 24, 2018 69

በአማራ ክልልም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚነሡ የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎችን ለአጭር ጊዜ እፎይታ ብሎ በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ መመለስ እንደማይቻል እና ጉዳዩ በሕግ አግባብ እና በሀገራዊ ምክክር ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የወልቃይትን ጉዳይ እንደ አብነት በማንሣት በትግራይም ሆነ በአማራ ክልል በኩል የሚነሡ ጥያቄዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ዘላቂ መፍትሔው የሁለቱንም ሕዝቦች ጥቅም በማይጎዳ፣ በውይይት እና ሁለቱም አሸናፊ በሚሆኑበት ሕገ-መንግሥታዊ መንገድ ካልሆነ መልሶ ለግጭት የሚዳርግ ቆይቶ የሚፈነዳ ቦምብ ይሆናል ብለዋል።

በሌላ በኩል ከውጡ ማግስት ጀምሮ በርካታ ዋና ዋና ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹ ሲሆን በዚህም በፓርቲ ውስጥ የነበረውን -ዴሞክራሲያዊ አሠራር ማስተካከል እና የክልሎችን ራስን የማስተዳደር መብት ማክበር ተችሏል ብለዋል።

በተጨማሪም በመንግሥት ተቋማት አካታችነትን ማረጋገጥ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በካቢኔ እና በፖለቲካ ምኅዳር ማሳተፍ እንዲሁም አግላይ የነበሩ  ትርክቶችን ማረቅም ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል እንደሆነ አስረድተዋል።

በበረከት ሽመልስ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: