Search

ከዕውቀት ተቀባይነት ወደ አምራችነት የነገዋን ኢትዮጵያ የሚገነባው የዲጂታል ትውልድ

ሓሙስ ነሐሴ 07, 2018 62

በቅርበት የምንጠቀማቸው የቴክኖሎጂ ግብአቶች የፈጠራ ክህሎት ማዳበሪያ መንገድ እየሆኑ ነው። ዓለም በቴክኖሎጂ ፍጥነት እየተለወጠች በመሆኑ፣ በዚህ የለውጥ ዘመን የአንድ ሀገር ተወዳዳሪነት የሚወሰነው ዕውቀትን ወደ ቴክኖሎጂ፣ ቴክኖሎጂን ደግሞ ወደ ምርታማነት በመቀየር በምትፈጥረው አቅም ላይ ነው።

ኢትዮጵያም በዚህ የዲጂታል ለውጥ ጉዞ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ትውልድን ብቻ ሳይሆን፤ ቴክኖሎጂን የሚፈጥር፣ የሚያድስ እና የራሱን መፍትሄ የሚያመነጭ ዲጂታል ትውልድ የማፍራት ተልዕኮ ሰንቃ ሰፊ ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች።

ይህንን ራዕይ ከሚያጠናክሩ ትልልቅ የሰው ሀብት ልማት ተነሳሽነቶች መካከል "የአምስት ሚሊዮን ኮደሮች" ስልጠና ቀዳሚው ነው።

በየዘርፉ ያሉ የክህሎት ስልጠናዎች ሀገራችን ያስቀመጠችውን የኢኮኖሚ ራዕይ ለማሳካት ዋነኛ ማፋጠኛ ሞተር ናቸው። የኮዲንግ ሚሊዮን ሰልጣኞች ሀገራዊ ችግሮችን የሚፈቱ የራሳቸውን የቴክኖሎጂ ስታርትአፖች (Startups) በመመስረት ስኬታማ እንዲሆኑ ትልቅ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።

ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ወደ ፈጣሪ ተሳታፊ፣ እንዲሁም ከዕውቀት ተቀባይ ወደ ዕውቀት አምራች የሚደረገው የዚህ ታላቅ ጉዞ መነሻ ከሩቅ ሳይሆን አሁን በቅርበት በእጃችን ካለው ቴክኖሎጂ ሆኗል።

በልዩ እሸቱ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: