የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ከሰኞ ከሰዓት ጀምሮ ውጤታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ይፋ በሚያደርገው ድረ ገጽ ገብተው ማየት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ባገኙት ውጤት ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች፣ ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት ውጤቱ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ከ5 እስከ 6 ቀናት ጊዜ እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።
ተማሪዎች እና ወላጆች በተሰጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ውጤታቸውን መመልከት እና ቅሬታ ካላቸውም በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ማቅረብ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በሐና ምንዳሁን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: