Search

የሻምፒዮኑ አርሰናል የክረምት ወራት ዝውውሮች

ዓርብ ነሐሴ 22, 2018 248

የክረምቱ ወራት የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት የፊታችን ማክሰኞ ይዘጋል።

ተጀምሮ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች በተካሄዱበት እና ከዛሬ ጀምሮ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሚካሄዱበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ ክለቦች ተጫዋቾችን በማስፈረም ስብስባቸውን ማጠናከራቸውን ቀጥለዋል።

የ2025/26 ሻምፒዮኑ አርሰናል ቪኒሲየስ ጁኒየርን ከመሰለ ግዙፍ ዝውውር ጋር ስሙ ተያይዞ ቢቆይም፣ ተጫዋቹ በማድሪድ ለመቆየት መስማማቱን ተከትሎ የአርሰናል ፍላጎት አልተሳካም።

ሆኖም አርሰናል ከውሰት ከመለሳቸው እና በቋሚነት ካስፈረማቸው ተጫዋቾች ጎን፣ ሦስት ዐበይት ዝውውሮችን አሳክቷል። ኤዝሪ ኮንሳን ከአስቶንቪላ፣ ክርስቶስ ዞሊስን ከክለብ ብሩዥ እንዲሁም ብሩኖ ጊማሬሽን ከኒውካስል ወደ ኢሚሬትስ አምጥቷል።

በሻምፒዮንነት ጉዟቸው ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተውን ሊሳንድሮ ትሮሳርድ ለቤሽኪታሽ መሸጣቸውን ጨምሮ፣ 6 ተጫዋቾችን ደግሞ አሳልፈው ሰጥተዋል።

አርሰናል በአዲሱ የውድድር ዓመት ውጥኑ ከ22 ዓመታት በኋላ የተመለሰበትን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ማስቀጠል ብቻ አይደለም።

በተደጋጋሚ ጫፍ ደርሶ የሚመለስበትን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊነት ለመጀመሪያ ጊዜ ማረጋገጥም ሌላኛው የቤት ሥራው ነው።

በእስካሁኑ ሂደት አርሰናል በዝውውር መስኮቱ የተጓዘበትን መንገድ እንዴት አገኛችሁት? ሐሳባችሁን አጋሩን።

በእድሪስ አሕመድ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: