የአፍሪካ ግዙፉ የአቪዬሽን ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደቡብ ምዕራብ ቻይና የምትገኘውን የቼንግዱ ከተማ ከአፍሪካ አህጉር ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ አዲስ የዕቃ ጭነት (ካርጎ) የበረራ አገልግሎት በይፋ ማስጀመሩን አስታወቀ።
ይህ አዲስ አየር መንገድ መከፈቱ በምዕራብ ቻይና እና በስፋት እየደገች ባለው የአፍሪካ አህጉር መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢኮኖሚ እና የኢንቨስትመንት ልውውጥ በከፍተኛ ደረጃ የሚያፋጥን እና የሚያጠናክር አዲስ የዲፕሎማሲ እና የንግድ ድልድይ ሆኖ ተመዝግቧል።
ይህ አዲስ የካርጎ በረራ መሥመር የሸቀጦችን እና የንግድ ቁሳቁሶችን እንቅስቃሴ ፈጣን እና ቀልጣፋ የሚያደርግ በመሆኑ፣ በሁለቱ ቀጣናዎች መካከል የሚደረገውን የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን ስትራቴጂያዊ የካርጎ በረራ መክፈቱ የአፍሪካ ዋና የሎጂስቲክስ እና የጭነት ማዕከልነቱን አጠናክሮ የሚያስቀጥለው ሲሆን፣ ለሁለቱም ወገኖች የንግድ ማኅበረሰቦች አዳዲስ የንግድ ዕድሎችን እና የገበያ ትሥሥሮችን የሚያስፋፋ ሀገራዊ እና አህጉራዊ ስኬት ነው።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: