የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን አከናውኗል።
በዚህም ቁጥራቸው ከ350 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ለአቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚያስችል የመሠረት ድንጋይ ተቀመጧል።
ድጋፉን ያስረከቡት በኢቢሲ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ማዕረግ የቴሌቪዥን ዘርፍ ኃላፊ ዘላለም እንደሻው ናቸው።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ኢቢሲ ከይዘት ሥራዎች ባለፈ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣት አንዱ አካል ነው።
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ጌታሁን ፈንቴ እና የአነደድ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ጋሻዬ ባዩ የተደረገው ድጋፍ በችግር ውስጥ የቆየው የዞኑን ትምህርት ለማነቃቃት ትልቅ አቅም እንደሚሆን ጠቅሰዋል።
በሀብታሙ ድረስ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: