Search

የሰላም፣ የአንድነት እና የባህል ድምቀት የሆነው የጎቤ እና ሽኖዬ በዓል

ቅዳሜ ነሐሴ 23, 2018 190
የአዲስ ዓመት ዋዜማ ማብሰሪያ የሆነውና በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የ"ጎቤ እና ሽኖዬ" በዓል በህላዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በአንድነት እንዲከበር የቱለማ ኦሮሞ አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች ጥሪ አቀረቡ።
ዛሬ በአዲስ አበባ "ሆራ ፊንፊኔ" መግለጫ የሰጡት የቱለማ ኦሮሞ አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች፤ በዓሉ የኦሮሞ ወጣቶች ባህላዊ እሴቶቻቸውን የሚያንፀባርቁበትና አዲሱን ዓመት በፍቅር የሚቀበሉበት መሆኑን ገልጸዋል።
የቱለማ ኦሮሞ አባገዳ ጌቱ ተሊላ እንደገለጹት፣ በዓሉ ከነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ እስከ መስቀል በዓል ድረስ በመላው የኦሮሚያ ዞኖች እና ከተሞች በደመቀ ሁኔታ ይከበራል። በዓሉ የወጣቶች በመሆኑ፣ በባህላዊ ጭፈራዎች እና በምርቃት ታጅቦ የቆየውን ወግና ባህል በጠበቀ መልኩ ይከናወናልም ነው ያሉት።
በዓሉ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት በመሆኑ፣ ሁሉም ማኅበረሰብ በጋራ እንዲያከብረው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ይህንን የቆየ ባህላዊ እሴት እንዲያድግና ለትውልድ እንዲተላለፍ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበራረታ መሆኑንም አባገዳዎቹ እና ሀደ ሲንቄዎቹ በመግለጫቸው አንስተዋል።
በአሊ ደደፎ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: