Search

በኦሮሚያ ክልል የፍትህ ሥርዓትን ለማዘመን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አሠራር እየተተገበረ ነው

እሑድ ነሐሴ 24, 2018 166

በኦሮሚያ ክልል ፍትህን ለማስፈን እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር እየተተገበረ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው ዛሬ በአዳማ ከተማ መካሄድ በጀመረው 6ኛው የኦሮሚያ ክልል ዐቃቢያነ ሕግ ጉባኤ ላይ ነው።

በጉባኤው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጉዮ ዋሪ፤ በበጀት ዓመቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራር በመዘርጋት ዜጎች የተቀላጠፈ እና ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል።

ኃላፊው አክለውም ጉባኤው ተሳታፊዎች እርስ በርስ የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት እንዲሁም ለህብረተሰቡ የተሻለ የፍትህ አገልግሎት መስጠት የሚቻልበትን ሁኔታ የሚያመቻች መሆኑን ጠቁመዋል።

በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው በዚህ ጉባኤ ላይ ከ1 ሺህ 500 በላይ የፍትህ አካላት እና ተሳታፊዎች ታድመዋል።

በመሀሪ ዓለሙ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: