በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ የሚገኘው የሉና የተቀናጀ የእርሻ ልማት፣ የመንግሥት እና የግል ባለሀብቶች ትብብር ለኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን እያበረከተ ያለውን ተጨባጭ አስተዋጽኦ በግልጽ ያሳየ ነው።
ትጋት እና ዕውቀት ሲታከሉበት ምድራችን ምን ያህል በረከት ማፍራት እንደምትችል ይህ ማሳ ሕያው ምሥክር ሆኗል።
በአሁኑ ወቅት በዚህ ሰፊ የእርሻ መሬት ላይ ልዩ ልዩ የአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት እና የተለያዩ የተቀናጀ የግብርና ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛል።
በተለይም በከፍተኛ ጥራት እየተመረተ የሚገኘው የምርጥ ዘር ፓፓያ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ እና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ታስቦ እየለማ ያለ ሲሆን፣ ለአካባቢው ኢኮኖሚም አዲስ ተስፋ ፈንጥቋል።
የዚህ አልሚ ፕሮጀክት ስኬት ሌሎች ባለሀብቶችም በዘርፉ በስፋት ተሰማርተው ትርፋማ መሆን እንደሚችሉ ትልቅ ምሳሌ ነው።
በትዕግሥቱ ቡቼ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: