Search

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2019 በጀት ዓመት ከ15.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመስብሰብ እየተሰራ ነው፦ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን

ማክሰኞ ነሐሴ 26, 2018 146

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተካሄደው 5ኛው የታክስ ንቅናቄ  ክልሉ 2018 በጀት ዓመት 10.5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል።

2019 በጀት ዓመት ደግሞ 15.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመስብሰብ እየተሰራ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ አበበ ከዚህ ቀደም የተደረጉ የታክስ ንቅናቄዎች የክልሉን የገቢ አሰባሰብ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

አክለውም የግብር ከፋዮችን እንግልት ለማስቀረት በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ አሰራር ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በተያዘው በጀት ዓመት የክልሉን የገቢ አቅም በማሻሻል ሕዝቡን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ዜጎች ግብርን በወቅቱ በመክፈል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ግብርን የሚሰውሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

እንደ ሀገር ግብርን ለመሰብሰብ የሚደረገው ከፍተኛ ርብርብ ለውጥ እያመጣ መሆኑን እና በክልሉ የሚሰበሰበው ገቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ያነሱት አቶ አሻድሊ፤ የክልሉ መንግሥት ግብር ከፋዮችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በዚሁ በክልሉ በተካሄደው 5ኛው የታክስ ንቅናቄ መድረክ ላይ በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በነስረዲን ሐሚድ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: