Search

ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በአማራ ክልል የለሙ ከ35 በላይ ችግር ፈቺ ዲጂታል መተግበሪያዎችን መረቁ

ሓሙስ ነሐሴ 28, 2018 218

የአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ "ኤሌክትሮኒክስ ለዲጂታል 2030 መሠረት" በሚል መሪ መልዕክት በባሕር ዳር ከተማ ከነሐሴ 28 እስከ 30/2018 . ድረስ የሚቆይ ዐውደ ርዕይ እያካሄደ ነው።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ባለፉት ሦስት ዓመታት በክልሉ የለሙ 35 በላይ ችግር ፈቺ ዲጂታል መተግበሪያዎችን በዛሬው ዕለት መርቀዋል።

በርዕሰ መስተዳድሩ ተመርቀው ወደ ሥራ የገቡ የዲጂታል መፍትሔዎች መካከልም የፍትሕ ሥርዓቱን የሚያዘምኑ እና የተሻለ አገልግሎት የሚሰጡ፣ በኢንቨስትመንት እና በግብርና ዘርፎች፣ በቱሪዝም እና በሌሎች የለሙ እና እየለሙ ያሉ የቴክኖሎጂ የሽግግር ሥራዎችን ነው የመረቁት።

በመርሐ ግብሩም የኢፌዴሪ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላን (/) ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን በዲጂታል ዘርፉ ላይ ያተኮሩ የፓናል ውይይቶችም ይጠበቃሉ።

በተስፋሁን ደስታ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: