Search

"ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ ትሥሥርን ለማጠናከር በትኩረት እየሠራች ነው"፦ የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር

ሓሙስ ነሐሴ 28, 2018 134

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል ጠንካራ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትሥሥር ለመፍጠር የሚያስችሉ በርካታ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የንግድ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው፣ ባለፉት ዓመታት በመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና በድንበር ተሻጋሪ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ የተወሰኑ መሻሻሎች ታይተዋል።

ይሁን እንጂ፣ በሀገራቱ መካከል ያለው መደበኛ የንግድ ልውውጥ አሁንም ቢሆን አጥጋቢ ባለመሆኑ የጉምሩክ አሠራሮችን እና የድንበር ተሻጋሪ ንግድ ሒደቶችን ማዘመን እና ማስፋፋት አስፈላጊ ሆኖ ነው ተብሏል።

የቀጣናውን የንግድ ትሥሥር የበለጠ ለማጠናከር ከፖሊሲ ማሻሻያዎች ጀምሮ የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን ማፋጠን ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ዴኤታ ታዜር ገብረእግዚአብሔር እንዳስታወቁት፣ ኢትዮጵያ ቀጣናውን በንግድ እና በኢኮኖሚ ለማስተሣሠር የሚያስችሉ ሥራዎችን አጠናክራ ቀጥላለች። ከፖሊሲ ማሻሻያዎች አንሥቶ ለአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና አስፈላጊ የሆኑ አሠራሮችን በተግባር ላይ በማዋል ላይ ትገኛለች።

በተለይም ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማዕቀፍ መተግበሯ የኢትዮጵያን ዕድገት ከማሳለጡም በላይ፣ ለቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትሥሥር ትልቅ በር የከፈተ ነው። ይህ ጅምር ስኬት በቀጣናው ያለውን የንግድ እና ኢኮኖሚያዊ ትሥሥር ይበልጥ ለማጠናከር ቁልፍ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል።

በሳምሶን ገድሉ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: