Search

"የዮ ማስቃላ እሴቶች ለዘላቂ ሰላማችንና ብልጽግናችን" በአርባ ምንጭ ሲምፖዚየምና የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

ሰኞ መስከረም 11, 2019 30

በነገው ዕለት የሚከበረውን የጋሞ ሕዝቦች የዘመን መለወጫ " ማስቃላ" በዓልን አስመልክቶ፣ በጋሞ ዞንና በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት "የዮ ማስቃላ እሴቶች ለዘላቂ ሰላማችንና ብልጽግናችን" በሚል መሪ ቃል የሲምፖዚየምና የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልል፣ የዞን፣ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር፣ የወረዳና የከተማ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ከፓናል ውይይቱ አስቀድሞ ለበዓሉ የተዘጋጁ የተለያዩ ኤግዚቢሽኖችንና የባህል ትርኢቶችን በአካል ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን፣ የነባር እሴቶችና የባህል ሀብቶች ማሳያ የሆኑት እነዚህ ዝግጅቶችም ትኩረት ስበዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: