Search

የኢትዮጵያ የማድረግ አቅም ልዕልና እና የዓለም አቀፍ ተፈላጊነት አዲስ ምዕራፍ

ሰኞ መስከረም 11, 2019 31

ኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎችን በጽናት ተሻግራ የራሷን የልማትና የስኬት መስመር በግልጽ በማስመር ላይ ትገኛለች። አሁን የምንገኝበት የዕድገት ደረጃ ሀገራችን በዓለም አቀፍና አህጉራዊ መድረክ ላይ ያላትን የማድረግ አቅም በተግባር ያረጋገጠችበት እና ተፈላጊነቷን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳደገችበት ስትራቴጂካዊ ምዕራፍ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) “ትናንት ከነበርንበት ከፍ ብለናል እርሱ አይካድም፤ መድረስ ከሚጠበቅብን ግን ብዙ ይቀረናልሲሉ ያስተላለፉት መልእክት ኢትዮጵያ የደረሰችበትን ከፍታ የሚያሳይና ለቀጣዩ ጉዞ ከፍተኛ መነቃቃትን የሚፈጥር መርሕ ነው።

አክለውምኢትዮጵያ ወደፊት መሄድ የምትፈልግ ከሆነ ራሷን እንደ ሳይክል ነጂ ማየት አለባት፤ አንድ ሳይክል ነጂ ሁለት ነገሮች ይጠበቅበታል ወደፊት መሄድ እና ሚዛን መጠበቅሲሉ ያቀረቡት ፍልስፍና የዕድገትን ፍጥነት ከማክሮ-ኢኮኖሚ፣ ከማኅበራዊ ፍላጎቶች እና ከዘላቂ ሰላም ጋር አስተሳስሮ የመምራት ጥበብን ያሳያል።

ለዘመናት የቁጭት ምንጭ ሆኖ የቆየው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዛሬ የነጻነታችን እና የማድረግ አቅማችን ህያው ማሳያ ሆኗል።

በግድቡ አማካኝነት በጉባ ምድር የተፈጠረውና 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ የመያዝ አቅም ያለው ባለ 240 ኪሎ ሜትር ርዝመቱ የንጋት ሐይቅ፤ የአካባቢውን ሙቀት ወላፈን ወደ ነፋሻማ ኤኮ-ቱሪዝም ቀጣና ከመቀየሩም በላይ የምሥራቅ አፍሪካን የኃይል ትስስር እውን በማድረግ የኢትዮጵያን የጂኦ-ፖለቲካዊ ልዕልና እና ተፈላጊነት ከፍ አድርጎታል።

በተመሳሳይ በስንዴ ልማት፣ በሌማት ትሩፋት፣ በኢንዱስትሪና በቴክኖሎጂ የተመዘገቡት እመርታዎች የዚሁ የማድረግ አቅም ውጤቶች ናቸው።

የወደፊቷን ታላቅ ኢትዮጵያ ገጽታ የሚቀርጹ ሜጋ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያን በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ተወዳዳሪ እያደረጓት ይገኛሉ።

በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ለማስተናገድ የተነደፈውና የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው እየተፋጠነ ያለው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የሜጋ ኤርፖርት ከተማ ፕሮጀክት፣ የኢትዮጵያን የአቪዬሽን መሪነት ይበልጥ የሚያጠናክር ግዙፍ መሠረተ ልማት ነው።

በዓመት 3 ሚሊዮን ቶን ለማምረት የተነደፈው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና 3.5 ሚሊዮን ቶን ድፍድፍ ነዳጅ የማጣራት አቅም ያለው የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክቶችም ሀገራዊ ምርታማነትንና ራስን የመቻል አቅምን የሚያረጋግጡ ናቸው።

ከሩሲያውሮሳቶምእና ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ጋር በመተባበር በሁለት ሪአክተሮች እስከ 2 ሺህ 400 ሜጋ ዋት ኃይል ለማመንጨት የተያዘው የኑክሌር ቴክኖሎጂ ልማትም በሕክምና፣ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣት የኢትዮጵያን የወደፊት አቅም ወደ አዲስ ከፍታ ያሸጋግራል።

እነዚህ ተሰናስለው የተያዙ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የማድረግ አቅም እያደገ መምጣቱን እና በዓለም አቀፍ መድረክ ተፈላጊነቷ መላቁን የሚያስመሰክሩ ናቸው።

ኢትዮጵያ በጀመረችው የመደመር መንገድ ላይ በፍጥነትና ሚዛኗን ጠብቃ ወደፊት በምትገሰግስበት ጊዜ፣ የታለመው የበለጸገች እና በዓለም መድረክ የታፈረች ሀገር የመገንባት ራእይ በተጨባጭ እውን ይሆናል።

በለሚ ታደሰ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: