“መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፤ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን መፍጠር” በሚል መሪ ሐሳብ በኒውዮርክ እየተካሄደ የሚገኘው 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
በልዑክ ቡድኑ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ተሳትፈዋል፡፡
ኢትዮጵያ በጉባኤው ብሔራዊ ጥቅሟን እንዲሁም የአፍሪካን ጥቅም በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ በሚደረጉ ውይይቶች በንቃት እንደምትሳተፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
ኢትዮጵያ ከዋናው ጉባኤ ጎን ለጎን በሚደረጉ በርካታ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ስብሰባዎች ላይ እንደምትሳተፍም ተገልጿል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: