Search

የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን የወታደራዊ ሕይወት ጉዞ እና ፅናት የሚያንፀባርቀው "ድል ቁርሱ" መጽሐፍ ተመረቀ

ማክሰኞ መስከረም 12, 2019 47

የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወት ታሪክ፣ ልምድ፣ አመራር እና ጀግንነት ላይ የሚያጠነጥነው "ድል ቁርሱ" የተሰኘው መጽሐፍ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተመረቀ።

መጽሐፉ የግለሰብ ታሪክ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ከገጠሬዋ ኢትዮጵያ ክፍል ተነስቶ የወታደራዊ ሕይወትን በመቀላቀል ሀገር በፈተና ማዕበል በተናጠችበት ወቅት በፅናት የቆመ ታላቅ መሪን መንፈስ የሚያሳይ እና የሕይወት ውጣ ውረድን በጥልቀት የሚያስቃኝ ነው።

በዚሁ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሮፌሰር ዳኛቸው አስፋ፣ የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ዋና ዳይሬክቴር አቶ ዛዲግ አብራሃ እንዲሁም አቶ ብርሃኑ ደቦጭ በመጽሐፉ ላይ ምሁራዊ ሂስ እና ዳሰሳ አቅርበዋል።

በመጽሐፉ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ (/) ከፍተኛ የጦር ጄኔራል መኮንኖች፣ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

 

በሳዳት መሀመድሳኒ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: