የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም በአንድ ወር 15 የቀጠር ቀበሌዎች እና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታወቀ።
ኤሌክትሪክን በመላ ኢትዮጵያ ለማዳረስ ሲተገበር በቆየው በዚህ ፕሮግራም በአጠቃላይ 5 ሺህ 435 አባወራ እና እማወራዎች ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ተደርገዋል።
48.4 ኪ.ሜ መካከለኛ መስመር ዝርጋታ በተከናወነበት የገጠር ቀበሌዎች እና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ሲባል የተዘረጋውን መስመር ወደ ደንበኞች ደጃፍ ለማድረስ 162 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር በመዘርጋት 34 የተለያየ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች ጥቅም ላይ ውለዋል።
በነሐሴ ወር የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ከሆኑት የገጠር ቀበሌዎች እና መንደሮች ውስጥ ዘጠኙ ከግሪድ፣ ስድስቱ በፀሐይ ኃይል አማራጭ ተደራሽ የሆኑ መሆናቸውን አገልግሎቱ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2035 በሀገራችን ሁሉም ዜጎች ኤሌክትሪክ እንዲጠቀሙ ለማስቻል እየሠራ ይገኛል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: