Search

በአዳማ ከተማ በ1.8 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ዘመናዊ መናኸሪያ ተመረቀ

ረቡዕ መስከረም 13, 2019 141

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የመናኸሪያው የመጀመሪያ ምዕራፍ 8 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፤ ለግንባታውም 1.8 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል።

ዘመናዊና ምቹ ሆኖ የተገነባው ይህ መናኸሪያ ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው።

በተለይም ከዚህ ቀደም በትራንስፖርት ዘርፉ የነበረውን የአገልግሎት ጥራት ችግር በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀርፍ ተገልጿል።

መናኸሪያው በአንድ ጊዜ እስከ 400 ተሽከርካሪዎችን እና 30 ሺህ መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም አለው።

በአባዲ ወይናይ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: