የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የህወሓት ነባር አመራር ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ እና የጦርነት አባዜ በመቃወም ወደ ፌዴራል መንግሥት ገብተዋል።
ጄኔራል መኮንኑ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ በከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ ያገለገሉ ሲሆን፣ ህወሓት በሀገር ላይ ክህደት እስኪፈጽም ድረስ የመከላከያ መረጃ እና ዘመቻ ዋና መምሪያዎች ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።
ዕድሜያቸው ለውጊያ ያልደረሱ ሕፃናትን አስገድዶ በመመልመል ለጦርነት በመማገድ፣ የትግራይ ሕዝብን ስቃይ እያባዛ ያለውን የህወሓት እኩይ ሴራ በመቃወም ጄኔራሉ ከድርጅቱ መለየታቸው የሕገ-ወጡን የህወሓት ቡድን ሕልውና ማክተሙን ያሳያል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: