Search

በአራት ወራት ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ከቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “ የተቀየረው የመኖሪያ ስፍራ ምን ምን አካቷል?

ሓሙስ መስከረም 14, 2019 195
👉 በ11 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የተገነቡ G+8 የሆኑ ዘጠኝ (9) ብሎኮች 👉 በአራት ወራት ውስጥ የተገነቡ 960 ቤቶች 👉 ሰፊ የሥራ እድልን የሚፈጥሩ 371 የንግድ ሱቆች 👉 በውስጡ የህጻናት የመጫወቻ ስፍራ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ (የኳስ ሜዳ፣ ቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ የመረብ ኳስ፥ የሰውነት ማጎልመሻ ቦታዎች) 👉 ለነዋሪዎች የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ እና ለኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ 👉 የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ 👉 ዘጠኙም ብሎኮች ላይ የጋራ መጠቀሚያ ሰገነት፣ ሊፍት፣ የፍሳሽና የኤሌክትሪክ መስመሮች 👉 ቅጠል ተራ ለመኖር እጅግ ምቹ ያልነበረ፤ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥን፣ እጅግ የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ በአስከፊ የእሳት አደጋ የተጎዳ አካባቢ ነበር። ይሁን እንጂ “መርካቶ የበጎነት መንደር “አካባቢውን “ተራ” በሚል ስያሜ የተሰጣቸውን እንደ ቅጠል ተራ፣ ጭድ ተራ፣ ገብስ ተራ፣ ሳር ተራ፣ ቦንብ ተራ… ወዘተ ያሉ ጎስቋላ አካባቢዎችን ወደ ውብ አካባቢ የመለወጥ ጉልህ ማሳያ ነው።
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: