የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ከኖርዌይ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር አቶ ኦስሙንድ ኦክሩስት ጋር ተወያይተዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ 81ኛ መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን የተደረገው ውይይት በሱዳን እና በአፍሪካ ቀንድ ላይ ባሉ ሀገራት የሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሁለቱ ወገኖች በሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚደረጉ የተቀናጁ ጥረቶችን ለማጠናከር ያላቸውን ሐሳብ መለዋወጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: