Search

ታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ አቀንቃኝ ዳዊቴ መኮንን ከ27 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሩ ተመለሰ

ዓርብ መስከረም 15, 2019 152

“አን ዱፌን ጂራ” /Ani Dhufeen Jira/ በሚል ዘፈኑ የሚታወቀው አርቲስት ዳዊቴ መኮንን ከ27 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ ሀገሩ ተመልሷል።

ባለፉት ሥርዓቶች በሕዝብ ላይ ሲደርስ የነበረውን ጭቆና በዘፈኖቹ ሲታገል የቆየው አርቲስት ዳዊቴ፣ በተለይም በህወሓት መራሹ የኢሕአዴግ መንግሥት ሲደርስበት የነበረውን እንግልት በመሸሽ ከሀገር መውጣቱ ይታወሳል።

ዳዊቴ በዘፈኖቹ እንዳንጸባረቀው፤ በወቅቱ በነበረው ሥርዓት ጫና ከሀገር ተሰድዶ ለ27 ዓመታት በባዕድ ሀገር ለመኖር ተገድዷል።

አብዛኛዎቹ ዘፈኖቹ ከተጨባጭ ኩነቶች ጋር ተዛምደው ትርጉም የሚሰጡ ናቸው። ከበርካታ ዓመታት በፊት “አን ዱፌን ጂራ” (እነሆ መጥቻለሁ) ብሎ እንደዘፈነው ሁሉ፣ አሁን በብራ ከሚወደው ሕዝቡ መካከል ተገኝቷል።

በቆይታውም ከኢሬቻ በዓል ዋዜማ ጋር በተያያዘ “አን ዱፌን ጂራ” የተሰኘ ኮንሰርት በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ያዘጋጃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም እንደ አዳማ፣ ነቀምቴ፣ ሻሸመኔ፣ ጅማ እና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞችም “አን ዱፌን ጂራ” የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚካሄድ ከዳዊቴ መኮንን መረጃ ማግኘቱን ኦቢኤን ዘግቧል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: