አዲዳስ በለንደን ማራቶን አስደናቂ ታሪክ ላስመዘገቡት ለኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና ለኬንያዊው ሴባስቲያን ሳዌ በዋና መሥሪያ ቤቱ ልዩ ዕውቅና እና ክብር ሰጥቷቸዋል።
በ2026 ለንደን ማራቶን ሴባስቲያን ሳዌ 1:59:30 እንዲሁም ዮሚፍ ቀጄልቻ 1:59:41 በመሮጥ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች ገብተዋል።
ለረጅም ዓመታት የማራቶን የሁለት ሰዓት ገደብን መስበር በሰው አቅም ሊደረስበት የማይችል ተደርጎ ይታይ ነበር።
ዮሚፍ እና ሳዌ ይህንን ታሪክ በመቀየራቸው፣ በቀጣይ ማራቶንን በሁለት ሰዓት ውስጥ ማጠናቀቅ ይቻላል የሚል ጽኑ እምነት እንዲኖር አድርጓል።
የሁለቱ አትሌቶች የመሮጫ ጫማ አቅራቢ የሆነው አዲዳስም ለክብራቸው ሲል በዋናው መሥሪያ ቤቱ ስማቸውን እና የእግራቸውን ዐሻራ በክብር አስቀምጧል።
በአዲስ የሺዋስ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: