በአዲስ አበባ ታላቁን የመስቀል ደመራ በዓል በአብሮነት፣ በሰላም እና በድምቀት ለማክበር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በሰፊው እየካሄዱ ካሉ ዝግጅቶች አንዱ የሆነው የጽዳት ንቅናቄ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ ላይ የሁሉም ሃይማኖት ተቋማት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የመንግሥት አመራሮች እና የሥራ ኃላፊዎች፣ የጽዳት አምባሳደሮች እንዲሁም በርካታ የሃይማኖቱ ተከታዮች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት መገለጫ እንደመሆኑ መጠን፣ ቦታዎቹ ንጹሕ እና ለዕይታ የሚስቡ፣ በተለይም ለበዓሉ እንግዶች እና አክባሪዎች ምቹ እና ማራኪ እንዲሆኑ ትኩረት በመስጠት የተደረገው ጥረት፣ የኅብረተሰቡን የባለቤትነት ስሜት የሚያጎለብት እና በዓሉ በድምቀት እንዲከበር የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።
የጽዳት መርሐ ግብሮቹን ጨምሮ አዲስ አበባ ከተማ ለበዓሉ የሰጠችው ልዩ ትኩረት፣ የከተማዋን ገጽታ ይበልጥ ለማጉላት እንዲሁም ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊቶችን ጠብቃ ለትውልድ ለማስተላለፍ ዝግጁ መሆኗን የሚያሳይ መሆኑን ከአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: