Search

የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶች

ዓርብ መስከረም 15, 2019 184

መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

ከመስከረም 15 ቀን 2018 ዓ/ም ረፋድ ከ5:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡-

• ከ 22 ማዞሪያ ወደ መስቀል አደባባይ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች

• ከቦሌ ኤርፖርት ወደ መስቀል አደባባይ ደንበል ወይም ኦሎምፒያ ላይ እና ታች

• ከጎፋ ፣ በታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ

• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መሰቀል አደባባይ ለገሃር መብራት

• ከለገሃር ቴሌ ወደ ስታዲየም ንግድ ባንክ ክቡ ህንጻ መስቀለኛ

• ከቸርቸል ጎዳና ፣ በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት ላይ

• ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መስቀለኛ

• ከካዛንቺስ መብራት ወደ መስቀለኛ መቅረዝ ሆስፒታል የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል።

ነገ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ01-11-11-01-11 እና በ990 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: