Search

የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አዲሱ የዕውቅና ባህል፦ ከግብር ከፋዮች ክብር እስከ ባለብዙ ዘርፍ የሀገር ግንባታ

ዓርብ መስከረም 15, 2019 126

የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ-ግብርን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመሩት ስትራቴጂዎች፣ ራስን በመቻል፣ በፈጠራ እና በተቀናጀ ጥረት ላይ በመመስረት ባለብዙ ዘርፍ የሀገር ግንባታን እውን እያደረጉ ይገኛሉ።

እነዚህ አርቆ አሳቢ ፖሊሲዎች ግብርናን፣ ቱሪዝምን፣ አምራች ኢንዱስትሪውን፣ ቴክኖሎጂን፣ ጤናን፣ ትምህርትን፣ ማህበራዊ ደኅንነትን እና ተቋም ግንባታን በከፍተኛ ደረጃ በማጠናከር ለወደፊቱ ትውልድ የሚሻገር ጽኑ እና የበለጸገች ኢትዮጵያን የመገንባት አቅምን በከፍተኛ ደረጃ እያሳደጉ ነው።

ከኢኮኖሚ ማሻሻያው ጎን ለጎን፣ የግብር መሠረቱን ለማስተካከል እና የሕዝብ አመኔታን ለማጎልበት አዲስ የዕውቅና አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓትና የቅንነት ባህል ተተክሏል።

በዚህም በየበጀት ዓመቱ ከፍተኛ አፈጻጸም ያላቸው የፕላቲነም፣ የወርቅ እና የብር ደረጃ ግብር ከፋዮች በአደባባይ ይሸለማሉ፤ የከፈሉት ግብርም እንደ ኮሪደር ልማት እና ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ባሉ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ተጨባጭ ፍሬ ማፍራቱ በግልጽ እየተረጋገጠ ይገኛል።

ይህ የዕውቅና ባህል ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ብሎም ዘላቂ ለውጥ ላመጡ ግለሰቦችና ተቋማት የሚሰጠውን ምስጋና በላቀ ደረጃ አሳድጎታል።

ትጋትን ማወቅ፤ ሀገርን መገንባት!

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: