የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ፣ በአሜሪካ፣ ኒውዮርክ እየተካሄደ ካለው 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከተመድ የሰላም ኦፕሬሽኖች ምክትል ዋና ጸሐፊ ዣን-ፒየር ላክሮዋ ጋር ተወያይተዋል።
ምክትል ዋና ጸሐፊው በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላበረከተችው የላቀ አስተዋጽኦ ከፍተኛ አድናቆት ችረዋል።
ተወያዮቹ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ዘላቂነት ሰላምን ለማረጋገጥ የትብብር ማዕቀፍን እና የተቀናጀ አሠራርን ማጠናከር አስፈላጊ ስለመሆኑ አጽንኦት ሰጥተዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: