Search

አስቸጋሪ የክረምት ወር አልፎ የመጸው ወር በሚባበት ጊዜ የሚከበረው መስቀል የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ነው፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ቅዳሜ መስከረም 16, 2019 106

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፣ የመስቀል በዓል መስቀሉ ለ300 ዓመታት ከተደበቀበት የወጣበት፣ መልካም የምሥራች የተነገረበትና ብርሃን የተገለጠበት በዓል ነው ብለዋል፡፡

በአንድ ዘመን የተሳሳቱ ሰዎች የፈጠሩትን ጥፋት፤ በሌላ ዘመን የተነሡ ተቆርቋሪ ሰዎች አስተካክለውታል፣ ልክ እኛ የባሕር በርን ለማስተካከል እንደምንሠራው ነው ያሉት፡፡

አስቸጋሪ የክረምት ወር አልፎ የመጸው ወር በሚባበበት ጊዜ የሚከበረው መስቀል የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፣ በአንድ በኩል ችቦዎች ተደምረው ደመራውን ይገነባሉ ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ያሉ ሁሉ በተመሳሳይ ቀን፣ በተመሳሳይ አከባበር፤ እንደየብሔረሰቡ ባህል ተደምረው በዓሉን ያከብራሉ ነው ያሉት በመልዕክታቸው፡፡

 

“የጎመን ምንቸት ውጣ፣ የገንፎ ምንቸት ግባ” እንደሚባለው ሁሉ፣ 2019 ዓመት፣ አስቀድሞ መውጣት የጀመረው የኢትዮጵያ የችግርና የፈተና ምንቸት ተጠቃልሎ የሚወጣበትና የብልጽግና ምንቸት በየቤታችን የሚገባበት ዓመት እንደሚሆን አምናለሁ ሲሉም አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የችግርና የፈተና ምንቸት ተጠቃልሎ የሚወጣበትና የብልጽግና ምንቸት በየቤታችን የሚገባበት ዓመት እንደሚሆን አምናለሁ ሲሉም አመልክተዋል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: