የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የከተማችን ድምቀት ከሆኑ የአደባባይ በዓላት አንዱ ለሆነውና በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ለተመዘገበው ለመስቀል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳቸሁ ብለዋል።
በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በባህላዊ አልባሳቶቻችን ደምቆ፣ የቱሪዝም ስበት ሆኖ የሀገራችንን መልካም ገጽታ በሚያጎላ መልክ እንደሚከበር ገልጸዋል።
እንደ ወትሮው ሁሉ በዓሉን ስናከብር እንደ ደመራው በአብሮነት ተደምረን፣ በትብብር፣ በመተሳሰብ እና በፍቅር እንድናከብር መልካም ምኞቴን እገልጻለሁም ነው ያሉት።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: