Search

የሕዝባችን አንድነት የኢትዮጵያ ከፍታና ብሩህ መጻኢ ዋስትና ነው

ቅዳሜ መስከረም 16, 2019 85
እንጨት ተሰባስቦና ተያይዞ ሲነድ ታላቅ ብርሃንና ሙቀት እንደሚሰጥ ሁሉ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም በልዩነቱ አምሮ በአንድነትና በማህበራዊ ትስስር ሲደመር የሀገራችን የከፍታና የድል ብርሃን በላቀ ደረጃ ይበራል።
የመደመር እሴትና የሕዝባችን ፅኑ አቅም የሀገራዊ አንድነታችንን መሠረት የሚያጠናክር፣ የታሪካዊ ጉዟችንን ስኬት የሚያፋጥን እንዲሁም የወደፊት ብሩህ ተስፋችንን በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ ህያው ኃይል ነው።
ዛሬ ላይ የምናስመዘግበው እያደገ የመጣ ሀገራዊ ዕድገት፣ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እና የመሠረተ-ልማት ስኬቶች የዚህ የተቀናጀ የሕዝባችን ጥረትና የጋራ ትጋት ውጤቶች ናቸው።
ሁላችንም አቅማችንን፣ ዕውቀታችንን እና ጉልበታችንን ለጋራ ሀገራዊ አላማ ስናስተባብር፣ የትኛውም ተፈታታኝ ሁኔታ የሀገራችንን የዕድገት ጉዞ ማስቆም አይችልም። የኢትዮጵያ የነገዋ ከፍታና የስልጣኔ ማማ የሚረጋገጠው በዛሬው የታደሰ አንድነታችን እና ባልተቋረጠ ሀገራዊ መደመራችን ነው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: