የመስቀል ደመራ በዓል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በወረብ እና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል።
የመስቀል ደመራ በዓል ሕዝበ ክርስቲያኑ ፍቅር፣ አንድነትና መስዋዕትነትን ከእየሱስ ክርስቶስ የወረሰበት ዕለት በመሆኑ በአንድነትና በፍቅር በየዓመቱ ይከበራል።
ደመራ ማለት ደመረ፣ አከለ የሚል ትርጓሜ ያለው ሲሆን፣ ምዕመናኑ አንድነቱን እና ፍቅሩን የሚያጠናክርበት ዕለት እንደሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ይናገራሉ።
በዓሉ የቱሪዝም መስህብ በመሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው ዕለት እንደሆነም ይታወቃል።
በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ባለው የመስቀል ደመራ ሥነ ሥርዓት ሕዝበ ክርስቲያኑ ህብረ ዝማሬዎችንና ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን በመከታተል ላይ ይገኛል።
በጀማል አህመድ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: