Search

ከፍታችን ከታሪካችን በላይ ነው! ታላቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ!

እሑድ መስከረም 17, 2019 63

ኢትዮጵያ በነጻነቷ፣ በጥንታዊ ሥልጣኔዋ እና በታሪካዊ ልቅናዋ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅ ታላቅ ስም ያላት ሀገር ናት። ነገር ግን የሀገራችን የወደፊት ከፍታ እና እመርታ ከትናንት ታሪካችን በላይ እጅግ የላቀ እና ብሩህ እንዲሆን ታላቁ ሕዝባችን በጽኑ መሠረት ላይ እየሠራ ይገኛል።

ታሪካችን የመነሻ ጉልበታችን እንጂ ማቆሚያችን አለመሆኑን በተግባር በማረጋገጥ፣ አዲስ የመስፈንጠር እና የሥልጣኔ ማማ ላይ የመድረስ ዘመንን እውን እያደረግን ነው።

ዛሬ ላይ በሁሉም ዘርፎች የሚመዘገቡት የልማት ስኬቶች፣ የመሠረተ ልማት እመርታዎች እና የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የመደመርን እሴት በመያዝ በጥቅል ሀገራዊ አቅም እየተተገበሩ ያሉ ናቸው።

"ኢትዮጵያ ታቅዳለች፣ ትፈጽማለች!" የሚለውን ጽኑ መርሕ በመከተል የሚከናወኑት ታላላቅ ፕሮጀክቶች፣ የታላቁ ሕዝባችንን የማይበገር ጽናት እና የላቀ የአመራር ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ናቸው።

የትኛውም ፈታኝ ሁኔታ ሳይበግረን፣ ሀገራዊ ሉዓላዊነታችንን እና ልማታችንን አስተማማኝ በማድረግ ታላቋን ኢትዮጵያን ለወደፊቱ ትውልድ እናስረክባለን።

በታደሰ አንድነት እና ባልተቋረጠ ጥረት የኢትዮጵያን የከፍታ ዘመን እውን እናደርጋለን!

በጌቱ ላቀው

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: