Search

የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት 1ኛ ጉባዔ ነገ ይካሄዳል

እሑድ መስከረም 17, 2019 157

የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት 1ኛ ጉባዔ ታሪካዊ እና አስፈላጊ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እንደሚሆን የጨፌው አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ሳዓዳ አብዱራህማን ገለጹ።

በ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ በአብላጫ ድምፅ ያሸነፈው ብልጽግና ፓርቲ የክልሉን መንግሥት እንዲያቋቁም በሕግ የተደነገገ በመሆኑ፣ ነገ የሚካሄደው የጨፌው የመጀመሪያ ጉባዔ የክልሉን መንግሥት አመሠራረት እና ለጉባዔው የተያዙ የተለያዩ አጀንዳዎችን በመመልከት እንደሚያጸድቅ አፈ-ጉባዔዋ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚህም መሠረት ጉባዔው ነገ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በአዳማ ከተማ በጨፌ አዳራሽ በይፋ የሚከፈት ሲሆን፣ በተያዙት አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በሳዳት መሐመድሳኒ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: