Search

ጨፌ ኦሮሚያ አቶ አብዱልሰላም ዋሪዮን አፈ ጉባኤ አድርጎ መረጠ

ሰኞ መስከረም 18, 2019 144
ጨፌ ኦሮሚያ1ኛ ዓመት የ7ኛ የሥራ ዘመን የመጀመሪያ ጉባኤውን እያካሄደ ባለበት ወቅት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤ ሾሟል።
በዚሁ መሠረት፦
አቶ አብዱልሰላም ዋሪዮ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ
ወይዘሮ ዘምዘም ሻሎ የጨፌ ኦሮሚያ ምክትል አፈ ጉባኤ በማድረግ ሹመታቸውን አጽድቋል።
ሁለቱም አፈጉባኤዎች ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
ይህንን ተከትሎ የቀድሞዋ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሰዐዳ አብዱረህማን አዲሱ ለተመረጡት አፈ ጉባኤ አቶ አብዱልሰላም ዋሪዮ የሥልጣን ርክክብ አድርገዋል።
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: